Contact me

  • Contact me via hawiti@yahoo.com or hawiolani@gmail.com

Sunday, May 4, 2014

ለኦህዴድ ባለስልጣናትና አባላት; ለኦሮሚያ ፖሊስ አባላት፣ etc

  
From Qeerroo Oromia
ለኦህዴድ ባለስልጣናትና አባላት፣
ለኦሮሚያ ፖሊስ አባላት፣
ለኦሮሚያ አድማ በታኝ ፖሊስ አባላት፣
ለኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ፖሊስ አባላት እንዲሁም
የፌዴራል ፖሊስ አባል ለሆናችሁ የኦሮሞ ልጆች እንዲሁም በወያኔ መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ለሚትገኙ ወገኖች በሙሉ
እናንተስ ከየትኛው ወገን ናችሁ!?
ይህንን ወቅታዊና ታርካዊ ጥያቄ ትመልሱ ዘንድ ጊዜው ደረሰ። እናንተ የሚታገለግሉት አሸባር ቡድን ጠላትነቱን በገሃድ ባረጋገጠ መልኩ ህዝባችሁን በገዛ ሃገሩ ላይ በአልሞ ተኳሽ ነፍሰገዳዮች ጥይት ሲያስረሸን ከዓይናችሁ ኣልፎ የድፍን ዓለም መነጋገሪያ ሆኗል። ከዚህ ህዝባችሁ ላይ ከተቃጣ ወደር የለሽ የጂኖሳይድ ጭፍጨፋ ተሳታፊነት ራሳችሁን እንዲታቅቡ፤ እንዲሁም ይንን የዳግማዊ ነፍጠኞች ወረራን ለመቀልበስ ይቻል ዘንድ ከህዝባችሁ ጎን በመሆን ሰልፋችሁን እንዲታስተካክሉ ታሪካዊ ጥሪ ቀርቦላችኋል።
ከዚህ በፊትም በህዝባችሁ ላይ ስደረግ የነበረውን መሰል ጭፍጨፋና ፈርጀ ብዙ ጭቆና ተባባሪ እንዳትሆኑ ፣ ከተቻለ ደግሞ ከህዝባችሁ ፍላጎት ኣንጻር እንዲትሰለፉ ህዝባችሁ ተመሳሳይ ጥሪዎችን ስያቀርብላችሁ መቆየቱ ይታወሳል። ሆኖም ግን በወቅቱ ለዚህ ሕዝባዊ ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ ባለመስጠታችሁ ይባስ ብሎም ተሳታፊ ሆኖ በመገኘታችሁ የኦሮሞ ህዝብ ለአሳቃቂ እልቂት ተዳርጓል።
ይህ ተደጋጋሚ ጭፍጨፋና ጭቆና የበዛበት ህዝብ ራሱን ለመከላከልና ብሔራዊ ነፃነቱን ለመጎናጸፍ ያለዉን ብቸኛ መንገድን በህይዋቱ ቤዛ ተያይዞታል።
ታላቁ የኦሮሞ ህዝብ በዳግማዊ ነፍጠኛ ኃይሎች እየደረሰበት ያለውን አሰቃቂ ጥቃት በመመከት ለትግሉ ያለውን ጽናት ና ቁርጠኛነት በውል አራጋግጧል። ይህ ህዝባዊ ንቅናቄ ለመጨረሻ ግቡ እስኪ በቃ ድረስ አጠቃላይ ሕዝባዊ ኃይሉን በማቀናጀት በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ለህዋታቸው ሳይሳሱ የሚተጉ ኣእላፍ የቁርጥ ቀን ልጆቹን ኣሰልፏል።
በመሆኑም ከላይ በተጠቀሰዉ መዋቅር ዉስጥ የሚትገኙ የኦሮሞ ልጆች፣ በተለይ ደግሞ የወታደራዊና ፖሊሲ አባላት ለሆናችሁ ታጣቂ ኃይሎች ህዝባችሁን የማዳን ብሔራዊ ግዴታን ትወጡ ዘንድ እነሆ ይህ ታሪካዊ ጥሪ በዲጋሚ ቀርቦላችኋል። ስለዚህ በመፍረስ ላይ የሚገኘውን አሸባሪ ሥርዓት በመልቀቅ ለዚህ ብሔራዊ ጥሪ ፈጣንና ተግባራዊ ምላሽ በመስጠት ራሣችሁን ከተጠያቂነት እንዲታድኑ ይሁን!
ዘለዓለማዊ ክብር ለተሰው ንጹሃን የኦሮሞ ተማሪዎች!!

No comments:

Post a Comment