Contact me

  • Contact me via hawiti@yahoo.com or hawiolani@gmail.com

Tuesday, February 24, 2015

Abdi Fiixee responds to Tedros Adhanom regarding Baritu



ዉሸትን መዋሸት ባለንበት ቦታ ብቻ ብንዋሽ አይሻልም??!! እንዲህ አይነት ቅሌት አንድ ተማርኩ ከሚል ሰዉ አይጠበቅም :: አቶ ቴዎድሮስ (ይቅርታ ዶክተር) ማለቱ ከብዶኝ ነዉ አቶ ያልኩኝ :: በሪቱ ገንዘቡን ያገኘቺበትን ትክክለኛ ታሪክ ቢነግሩን ያስመሰግናቸዉ ነበር:: ሌባ ለአመሉ ዳቦ ይልሳል ሆነና ነገሩ ይህንን እንኩአን እዉነቱን ሊነግሩን አልፈለጉም:: የበሪቱን በጎነት እና አስተዋይነትን ወደ ርካሽ ፖሎቲካ አዞሩትና እንዴት ብሎ መጠየቅ ልማዱ ያልሆነውን ህዝብ "በቅርቡ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳድራ 20 ሚልዮን የአውስትሬልያ ዶላር ተሸለመች" ብለዉን እርፍ:: ደግነቱ ኑሮአችን ደደቢት አይደለም:: ቅሌት:: በሪቱን ለማግኘት ባደረኩት ሙከራ ከጎሮቤትም ሆነ ከቅርብ ቤተዘመድ ያገኘዉት ምላሽ የ20 ሚሊዮን ዶላሩን ታሪክ እና በሪቱ አሸነፈች ስለተባለዉ አዋርድ የሚያዉቁት ነገር እንደሌለ ነዉ:: ነገሩን ሳሳጥረዉ:: እዉነቱ ወዲህ ነዉ:: ነገሩን የመልቦርን ነዋሪ እና በሪቱ ጃለታን በቅርበት የምያዉቃት ጃራ ቦሩ (jaarraa boru) እንዲህ ይገልፀዋል::
ታሪኩ እንዲህ ነው᎗ ባሪቱ ጃለታ(ከመሃመድ አህመድ እና ከክሚያ የተወለደች: የምልኬሳ እና ዳሜሳ እህት:) ከምትኖርበት ሜልበርን ልዩ ስሙ ወራቢ (Werribee) ከምባል ከተማ ለእረፍት ከቤተሰቦችዋ ጋር ሃገር ቤት ሄዳ በነበረችበት ወቅት በመንግስት ምንም ትኩረት ያልተሰጠበትን የጋራ ሙለታን አከባቢ ትምህርት ቤቶች ለመጎብኘት እድሉን ታገኛለች:: ያንን ጉብኝት ካደረገች በኋላ መንፈሷ እረፍት ያጣል:: ነብሷ ትጨነቃለች:: ወደምትኖርበት ሜልበርን (ወራቢ) ስትመለስ በዚሁ ጉዳይ ትታመማለች:: ትምህርቷን መከታተል ይሳናታል:: በየሳይካያትሪስቱ ብትወሰድ ለመንፈሷ ጭንቀት ምንም መፍትሔ ታጣ:: በመጨረሻም በሽታውን ያልተናገረ መፍትሄ አያገኝም በምለው ፕሪንስፕል በመመራት ለትምህርት ቤቷ ፕሪንስፓል (ዳይሬክተር) "ኢትዮጵያ ያሉት ልጆች በሚያፈስ ቤት ውስጥ እንደዚያ አፈር ላይ ተቀምጠው በተጨናነቀ ሁኔታ ሲማሩ አይቼ ደስታ ራቀኝ፣ እንቅልፍ አጣሁ፤ ምግብ እንኳ መብላት አልቻልኩም::" ብላ ስታለቅስባቸው ጊዜ የተለያዩ ገንዘብ የማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች ተካሂዶ የተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑድርጅቶች ተረባርበው የዚህችን ሲበዛ ሰብዓዊነት የተሞላባትን ታዳጊ ወጣት መንፈስ ለመታደግ ባሳዩት ርብርቦሽ አንድ ትምህርት ቤት ለመስራት የሚያስችል ፈንድ ይገኝላታል:: ታዲያ ዶክተሩ እንደዚያ በስንት እንባ፣ ህመም እና ደጅ መጥናት የተገኘውን ገንዘብ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ከውጭ ለሚጎበኛቸው እነኒያ በመንግስት ቸል የተባሉት ትምህርት ቤቶች ምን ያህል ሰዉን እንደሚያስለቅሱ ላለማንሳት እና ፖለቲካቸውን ለማሳመር እንዲመቻቸው ነው የሃያ ሚልዮኑን ቲዎሪ ይዘው ከች ያሉት:: ክፋቱ ግን ዘመኑ እነርሱ ደደቢት በረሃ ከገቡበት ዘመን የተሻለ የመረጃ እና የመገናኛ ምንጮች መኖራቸውን አለማወቃቸው ነው:: ድፍን የሜልበርን ህዝብ የሚያውቀውን ታሪክ መልኩን ለመለወጥ ፈለጉ:: ለነገሩ ትግራይ ውስጥ ካልሆነ በሌላ ክልሎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች አይደል እዚህ አገር ተወልዶ ያደገዉን ህጻን ያገር ውስጡንም አዋቂ ያስለቅሳል ምንም ለማድረግ አቅም ይጣ እንጂ:: የሆነ ሆኖ ዶክተሩን ሳላመሰግናቸው ላልፍ የማልፈልገው ግን ፈንዱን ወደ ትግራይ ሳያዞሩ እንደታቀደው ወደ ጋራ ሙለታ እንዲላክ መወሰናቸውን ነው:: በሪቱን እንኳን ደስ ያለሽ ልንላት ይገባል:: ያበባ እቅፍ ቱላማሪን አየር ማረፊያ ይጠብቃታል:: ዶክተር እርስዎን ግን ታዘብናችሁ:: ድግሪዎ ይመርመርልን! ቅቅቅ

No comments:

Post a Comment