Contact me

  • Contact me via hawiti@yahoo.com or hawiolani@gmail.com

Monday, February 23, 2015

በአዲስ አበባ ዙሪያ በናዝሬት/አዳማ እና ደብረዘይት ማስተር ፕላኑን የሚቃወም ቅስቀሳ ወያኔን አስጨንቆታል

መላው ኢትዮጵያውያን ለሚደረገው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ከጎናችን እንዲቆሙ ሲሉ አስተባባሪዎች ጠይቀዋል::ከመሃል ሃገር ከሚገኙ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች የደረሱን መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በወጣቶች ማህበር አስተባባሪነት በአዲስ አበባ ዙሪያ በናዝሬት/አዳማ እና ደብረዘይት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም እንዲሁም የወያኔው ጀሌ አባይ ጸሃዬ የሚባለው የተናገረውን ጸረ ሕዝብ አፍራሽ አነጋገር በመቃወም ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ቅስቀሳ እየተካሄደ መሆኑ ተጠቁሟል::ይህ ቅስቀሳ ወያኔን አስጨንቆ የያዘው ሲሆን ሊያስቆመው የማይችል ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ አመጽ ይቀሰቀሳል የሚል ስጋት አስከትሏል::
ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ክልሎች ላይ በተደረገ ተቃውሞ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን የተቹ የተቃወሙ እና ጥያቄዎችን ያቀረቡ ስለገበሬዎች መብት አቤት ያሉ ወጣቶች ተገለዋል ታስረዋል ተደብድበዋል በአፋኝ ሃይሎች ተሰውረዋል::ይህ ቁስል ሳይጠገን የሕወሓት ጀሌዎች በሃዋሳ በተደረገ ስብሰባ ላይ ባደረጉት እብሪት የተሞላ ንግግር ልክ እናስገባለን ብለው መዛታቸው በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል::ይህንን ቁጣ ተከትሎ በአዲስ አበባ ዙሪያ ከፍተኛ የሆነ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማድረግ ህዝብን የማስተባበር ስራ እና የቅስቀሳ ስራ እየተሰራ በመሆኑ መላው ኢትዮጵያውያን ከአስተባባሪዎች ጎን እንዲቆም ጥሪዎች አስተባባሪዎቹ ጠይቀዋል::

 - See more at: http://www.oromiapress.com/%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5-%E1%8A%A0%E1%89%A0%E1%89%A3-%E1%8B%99%E1%88%AA%E1%8B%AB-%E1%89%A0%E1%8A%93%E1%8B%9D%E1%88%AC%E1%89%B5%E1%8A%A0%E1%8B%B3%E1%88%9B-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E1%8B%B0/#sthash.0KYmuVJi.dpuf

No comments:

Post a Comment