Contact me

  • Contact me via hawiti@yahoo.com or hawiolani@gmail.com

Monday, June 8, 2015

የሕወሓት መንግስት ስርዓቱን የከዱትን 9 የጦር መኮንኖች እያደነ ነው * መኮንኖቹ ኦነግን ተቀላቅለዋል እየተባለ ነው




Moonaa Leenjii Giddu Gala ABO.  From File
(ምንሊክ ሳልሳዊ) ከደቡብ ምስራቅ እዝ የከዱ ዘጠኝ የባሌ ክፍለሃገር ተወላጅ የሆኑ የሰራዊቱ መኮንኖችን ለመያዝ ማደኑን አንደቀጠለ አና አስካሁን ከኦነግ ኣማጽያን ጋር ተቀላቅለዋል ከሚባል ውጪ ያሉበት ቦታ ምንም ፍንጭ እንደሌለ ለጦር ሃይሎች መምሪያ የደህንነት ክፍል የመጣ መረጃ መጠቆሙን የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል::
በተለያዩ ጊዜያት ከባለፉት ሳምንት ጀምሮ ድንበር ዘለል ወረራ በኬንያ ላይ ያደረገው የወያኔ ሰራዊት ከኦነግ ኣማጽያን ጋር ጦርነት ገጥሞ አንደነበር ሲታወስ የከዱ የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ከኦነግ ኣማጽያን ጋር ተደባልቀው የወያኔን ሰራዊት አንደወጉ ቢገለጽም አስካሁን ድረስ የኦነግ ታጣቂ ሃይሎችን ያሉበትን ኣከባቢ ለማግኘት ኣለመቻሉን መረጃዎቹ ሲጠቁሙ ኣሉበት የተባሉ ኣከባቢዎችን በሃገር ውስጥ ደኖች ላይ ኣንደተለመደው አሳት በመልቀቅ አና ጎረቤት ሃገሮችን በመውረር በሃይል ለማዳከም ስራዎች አየተሰሩ አንደሆን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::
ሰራዊቱን ከድተው ወተዋል ከተባሉት ከፍተኛ መኮንኖች ውስጥ ሶስቱ ኮሎኔሎች የጦር መሪዎች መሆናቸው ሲታወቅ አነሱም
፩ = ኮሎነል ያሲን ሁሴን
፪ = ኮሎኔል ነገራ ኢደሳ
፫ = ኮሎኔል ኑሩ ኣስሊ ይገኙበታል::
የሰራዊቱ የዘመቻ እንቅስቃሴ መረጃዎች በጃቸው አንደሆነ የሚነገርላቸው የጦር መሪዎች መክዳት ከፍተኛ ድንጋጤ አንደፈጠረ ታውቋል፥፥ ይህ በእንዲህ አንዳለ በሶማሊያ አና በኢትዮጵያ ድንበር ኣከባቢ በወያኔ ሰራዊት እና በኦብነግ ኣማጽያን መካከል ግጭቱ የቀጠለ ሲሆን በክዐንያው ድርድርም አስካሁን የተገኘ ውጤት አንዳሌለ ታውቋል:

No comments:

Post a Comment