ቴዲ አፍሮ አሁንም ይዘባርቃል::
በምንሊክ በሄኒከን በበደሌ በብዙ ኦሮምያ ወጣቶች በቴዲ አፍሮና በጃዋር መሃከል ሲደረግ የነበረውን ጠብ የሚመስል የቃላት መአት አይቻለሁ:: እነዚህ ምንሊክን የሚቃወሙት እትዮፒያውያን ወንድሞቻችን ያሰቡት ተሳክቶ ተቃውሞዋቸውን በትክክል አሰምተው ሄኒከንን ሃሳቡን አሰርዘዋል:: አርቲስት ቴዲ አፍሮም በትክክል አፍሮ አይቼዋለሁ::
በየማህበራዊ ድህረ ገጾች ክርክሮችና አስተያየቶች በዝተው ለማየት ችያለሁ:: በተለይ የቴዲ አፍሮን ዝናና ክብር ለመጠበቅ ሲለፉ የነበሩ ጋዜጠኞችም ዌብ ሳይቶችም በጣም አሳዝነውኛል:: ፍጹም ለማመን የሚከብድ ስህተት እየሰራ ያለን አንድ ያልተማረ ተራ አዝማሪን ለመከላከልና ለማገዝ የተደረገው ሙከራ ፍጹም የጋዜጠኝነትን ስነምግባር ያልተከተለ እንዲሁም በጥልቅ ሲታይ ውስጡ ባለፉት አስከፊ ዘመናት የነበሩትን ጨፍጫፊዎችን ማምለክ የተያያዘ እንደሆነ ግልጽ ሆኖ ታይቷል::
እነዚህን ጽሁፍ የሚጽፉት ሰዎች የጋዜጠኝነት ሙያቸውን (ካላቸው ነው) በማይረባ ሳንቲምና ፍርፋሪ ሸጠው ከመሳደብና ከመጮህ በስተቀር በሰለጠነ መንገድ በሃሳብ ዙሪያ መከራከር የማይችሉ ያገነኑትን ምንሊክን እንኳን ተሳስቶ ነበር ለማለት የሚያንቃቸው መሆኑን አይቻለሁ:: ይህ ያለንበት ዘመን ደግሞ 2014 እንደሚባልና ይሄ የነሱ ተረት እንደማይሰራ ልነግራቸው ፈለግኩኝ:: ታዲያ በዚህ መሃል የታዘብኩትንና ፍጹም ያልተመቸኝን ነገር ነጥብ በነጥብ አስቀምጣለሁ::
· ከመጽሄቱ ነው ስህተቱ ወይስ ከቴዲ አፍሮ? ከመጽሄቱ ከሆነ እንዴት ዘፋኙ ያላለውን ቃል እንደ አርእስት ለመጠቀም ፈለገ? ቴዲ አፍሮ ያላለው ከሆነ ለምን ይሄ ሁሉ ሙግት ውስጥ ይገባልበቀጥታ ለምን ያንን የጻፈውን አካል ወይም መጽሄት አይከሰውም?
· ለመሆኑ የጦርነት ቅዱስ አለው? ቅዱስ ጦርነት የሚለው ይህ ቃል ከራሱ ከቴዲ ካልመጣ እዛው እንቁ መጽሄትን ከሶና አፋጦ እሱ እንዳላለው አሳውቆ ለምን ነገሩን አያበርደውም?
· ዘፋኙ ባለጌና ስድ ነው እጅግ አላዋቂና ፍጹም አወናባጅ ነው ላለማለት ይሄ ሁሉ የዲያስፖራ ዌብ ሳይት ሙሉ የኦሮሞን ህዝብ ወይም አንድ ጃዋር የሚባልን ሰው የሚቃወመው ለምንድነው?
· ቴዲ አፍሮ ፍጹም የማይሳሳት በጣም ድንቅ አእምሮ እንዳለው አድርጋችሁ የምታንቆለጳጵሱት ለምንድነው? ከልጁ የነፍሰገዳይ ማንነትስ እንዴት ተረሳችሁ?
· እንዲህ ያለ አሳፋሪ አባባል ከሱም ይሁን ከመጽሄቱ አካላት ሲወጣ አንድ ጃዋርንና ብዙ የኦሮሞ ህዝቦችን ስትቃወሙና ስትዘልፉ ለምን ቴዲንና መጽሄቱን ሁለተኛ እንዳይለምዳቸው እንኳን አትገስፁም? እውነት ለመጻፍ አይደል እንዴ የቆማችሁት?
· በመኪና ሰው ገጭቶ ገድሏል ሲባልም እሱን ከመጠየቅ ይልቅ ወያኔ በፖለቲካ ነው ያሰረው ስትሉ ነበር አሁንም ይሄ ጃዋር ትላላችሁ ለመሆኑ ይታወቃችኋል?
· በደሌ ይህንን ኮንሰርት የሰረዘው ምንም ጥበቃ ስላላገኘ ለደህንነት ሲባል እንደሆነ እንጂ ፍላጎቱ እንደነበረው ታውቃላችሁ ታድያ እናንተንና ቴዲ አፍሮን የሚያሳስበው ኮንትራቱ ሲዘረዝየሚገኘው ሳንቲም እንጂ የተከለከለበት ምክንያት አይደለም ማለት ነው?
· ይሄን ያህል ብር ኮንትራቱ ስለተሰረዘ ይከፈለዋል ስትሉ ምንም የማያሳፍራችሁ ለምንድነው? ይሄ ሁሉ ሺ ሰው ቴዲንና በደሌን አጨናንቆና አስመስክሮ ኮንሰርቱን ሲያሰርዝ እንዴት ከባድአጀንዳ እንደያዘ ማመን አቃታችሁ? አንድ ተራ አዝማሪ የሚያነሳው ሃሳብ በዚህ ሁሉ ሰው ሲጠላ እንዴት ነው የምታዩት? ነው ወይስ እናንተ ይሄንን ወሬ ስታባዙና ስታናፍሱ የሚከፈላችሁ ነገርአለ? ምን ይሆን?
· በአገሩ ከተሞች እንዳይሰራ እየታገደ በህዝቡ እንዲህ አይነት ተቃውሞ እየደረሰበት ቦይኮት እየተደረገ ያለ ዘፋኝን በምን አይነት መለኪያ ነው የምታሞጋግሱት?
· ፍቅር የፍቅር ጉዞ እያለ የሚያጭበረብር እና የሚያታልል ለራሱ አንዲት መፍትሄ ማምጣት የማይችል አዝማሪ እንዴት በሙሉ የተቃዋሚ ጋዜጠኛ ነኝ ባዩን የዌብ ሳይት ባለቤት ድጋፍ ሊያገኝ ይችላል? ይሄ ምናልባት አርቲስቱና ማናጀር ተብዬው እነዚህን ዌብ ሳይቶች እየደጎሙ በብር እንደያዙት ያስታውቃል ካለዛ እንዲህ አይነት ያፈጠጠ ወሬና አሉባልታ እየተጻፈ አዝማሪውን ለመከላከል ጥረት አይደረግም ነበር::
አጉል መኮፈስ እና አጉል ስለፍቅር ሲባል ከፈጣሪ የተላኩ ዘፋኝ ነኝ ሊል የሞከረበት ተረት ተረቱን እንዳነበብኩ ያስቀመጥኳቸው ደግሞ:
· ይቅር መባባል ጥሩ ነው ይልና ባሁኑ ሰአት ኦሮሞው ወጣትና አዋቂ የሚጠይቀውን የምንሊክን አምባገነንነት እና የምንሊክ ጨፍጫፊነትን አለማመን ምን የሚሉት እውቀት ነው?
· ምንሊክ በሰራው መጥፎ ስራ የተቆጣ ህዝብ ምንሊክ እየተባለ እንዲዘፈንና እንዲደለቅ አይፈልግም እንዲህ የሚደርጉትንም ይቃወማል የኔንም ቁስል እየቀሰቀሳችሁ አታስከፉኝ ይላል:: ታድያ በዚህ ዘመን እሺ የኔ ወንድም የኔ ኦሮሞው አካሌ ብሎ እንደመተው ለምን ጭራሽ ነገሩን ከፍቅር ማጣት ጋር ሊያይዘው ይሞክራል?
· ፍቅር እያሉ እንዲህ ያፈጠጠ የወንበዴ እና የቁጭ በሉ ስራ መስራት በህግ እንደነ ታምራት ገለታ እንደሚያስቀጣ አታውቁም እንዴ? ቴዲ አፍሮ የሚባል ዘባራቂ አዝማሪ በሚችለው የዘፈን ሙያው እንዲ አይነት ቀውስ ለመፍጠር በዚህ መሃል በሚገኘው ትርምስ እና አጋጣሚ እኔ ከፈጣሪ የተላኩኝ ነቢይ ነኝ ለፍቅር የመጣሁ መሲህ እያለ ሳንቲምና ዝና ማግኘት የሚፈልግ የድሮ ዘመን እርድናውን በዚህ ዘመን ሊሞክር የሚፈልግ ድንቁርና የተጠናወተው ተራ አዝማሪ መሆኑን ካልነገርነው ማን ሊነግረው ነው?
· ምንሊክ ጨፍጫፊ ስለነበር አልወደውም የሚል ሰው እንዴት ነው ችግሩ በፍቅር የሚፈታው? ምንሊክ እያሉ በመዝፈን? ወይስ የወገኔን ቁስል አልቀሰቅስም ብሎ ምንሊክን እጅግ ባለማወደስ? ቴዲ ፍቅር እያሉ ፉገራ በጣም ተመችቶታል ምክንያቱም ፍቅር የሚለው ቃል እግዚያብሄር የሚለውን ትርጉም ስለሚያሰጥ ግን ፍቅርን የሚያቅ ቢሆን ድሮም ሰው ገጭቶ አያመልጥም አሁንም ወንጀለኛና ጨፍጫፊን አያሞጋግስም ነበር::
· ፈጣሪ ለዚህ ትውልድ በማሰብ ለፍቅር ብሎ ነው የላከኝ ብሎ በዚህ ዘመን ሊፎግር የፈለገን ዘፋኝ ማን ጸጥ ይለዋል? እነ ጃዋር አዲሱ ትውልድ መሆናቸውን ቴዲ ረሳው እንዴ?
· ”ህይወት የሚቀጥለው፣ ካለው ነገር ላይ በመነሳት ነው፡፡” የተምታታበትና ግራ የተጋባው ቴዲ አፍሮ የሚያወራው በራሱ በጣም ይቃረናል—— የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ ደሞ ይለናል::
· ”ፈጣሪ በየትውልዱ የራሱን ድምጽ ያወጣል። የትውልዱን ድምጽ በኔ አድርጐ ማውጣቱን አምናለሁ፡፡” ብሎ ሲዳፈር በጋዜጠኞች የሚታገዘው 2006ዓ.ም መሆኑን ረስተውታል እንዴ?
· አፍሪካን ሊወክል በህብረት ዘፈን ሰራ ተብሎ ዜናውን ለማረሳሳት ያየነው ዘፈን ላይ እንኳን ሊዘፍን ምንም የአጃቢ ቦታም እንዳላገኘ ለማየት ችያለሁ:: ለብቻው ነጥዬ ልሰማው ብፈልግምአንዲት ቃል አጥቼበታለሁ እንኳንስ ሊያኮራኝ ይቅርና ተራ ዘፋኝ መስሎ ሳየው አሳዝኖኛል ምናልባት ሌላ ቦታ እያወናበዱ መዝፈን እንደማይቻል አያውቅ ይሆናል::
ጋዜጠኞችም ከሰው ጥያቄዎችን ለምን እንደማትጠይቁት በጣም አስተውለናል ፊት ለፊት ጠይቁት እና መልሶችን ከአንደበቱ እንስማው ዛሬ ይዘባርቃል ነገ ደግሞ እኔ አላልኩም ይላል:: ዛሬ ሰውይገጫል ነገ ደሞ መንግስት አሰረኝ ይላል:: እንዲ አይነት አጭበርባሪ ነገ ደግሞ ነቢይ በአገሩ አይከበርም እንደሚል አልጠራጠርም::
ሰላም ሁኑ በፍቅር ስም ከሚያደናቁሩ ይጠብቃችሁ::
ቴዲ አፍሮ ነቢይ ነኝ ስሙኝ ሊል የፈለገበትን ቃለ ምልልስ አንብቡት ነገ ደግሞ አላልኩም ማለቱ አይቀርም:: ቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂ….
በሳምንቱ መጨረሻ ቴዲ አፍሮ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ቆይታ ነበረው፡፡ በሁለት ክፍል የተደረገውን ቃለ-ምልልስ የመጀመሪያ ክፍል እነሆ ፡)
“ከወረስነው ቂም ይልቅ የምናወርሰው ፍቅር ይበልጣል”
“ፈጣሪ በየትውልዱ የራሱን ድምጽ ያወጣል”
“ፍቅር ያሸንፋል– የኔ ሳይሆን የትውልድ ድምጽ ነው”
“እዳ አለ የምንል ከሆነም፤ እዳ የሚከፈለውና የሚሸፈነው በፍቅር ብቻ ነው
“ከታሪክ ከወረስነው ቂም ይልቅ የምናወርሰው ፍቅር ይበልጣል”
የፍቅር ጉዞ ከሚለው ሃሳብ እንጀምር፡፡ መነሻው ምንድነው?
“አቦጊዳ ብዬ፣ ፊደል “ሀ”ን ቆጥሬ፤
የፍቅርን ትርጉም ለልቤ አስተምሬ፣
ይዤሽ በአኮፋዳ እንደቆሎ ተማሪ፣
አቦጊዳ ልበል የፍቅር ጀማሪ…”
የፍቅርን ትርጉም ለልቤ አስተምሬ፣
ይዤሽ በአኮፋዳ እንደቆሎ ተማሪ፣
አቦጊዳ ልበል የፍቅር ጀማሪ…”
እንዲህ ነው የኔ የዘፈን ህይወት የሚጀምረው። አሁን የፍቅር ጉዞ ላይ ደርሷል፡፡ ሁላችንም፣ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ውስጥ እናልፋለን። ብዙ ቅሬታና ብዙ ደስታ፣ ብዙ ትክክል የሆኑ ነገሮችና ብዙ ትክክል ያልሆኑ ነገሮችአሉበት - ያለፍንበት ታሪክ፡፡ ትልቁ ነጥብ፣ ካለፍንበት ታሪክ ተነስተን ለሚቀጥለው ጊዜ ምን እናድርግ የሚለው ነው፡፡ ያዘንበትን ነገር በይቅርታ ሰርዘን፣ የወደድነውን ነገር ደግሞ አሳድገን ለመጓዝ፣ ትልቁ መድሃኒት ፍቅር ነው፡፡ይቅር ተባብሎ የቀድሞ ስህተቶችን ለማስተካከልና በህብረት ተጠራርቶ የቀድሞ
Duros Ka komche na ka komata min yitabakal, komata nachu sinilachaw aydelem yasalamon nagad yanugusoch zer nen yiluhal, asafari shash labash nigusachu idet mota sinilachaw, idmelikun si shash yamotaw le hizbu tasawito new yiluhal, bamin mote sinilachaw zim yiluha ba abalazer bashita mamotun sila miyakut.......are sintun.........
ReplyDelete